የሀያ ዘጠኝ አመት ኒጄርያዊቷ ሚያና ናሳን ተቀላቀለች

ሙሉ ስሟ ዶክተር ፈዲጂ ዙዋና ሚያና ስሆን ተወልዳ የደገችው በኒጄር ዚንደር ውስጥ ነው። በትምህርት ጉዞዎ ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት አንዳንድ ክፍሎችን ዘላለች። የሁለተኛ ደረጃ ድግሪ የያዘችው ገና በ16 አመቷ ነበር። ታድያ ሁሌም እንደምትለው ለዚህ ደረጃ ደርስኩት “ወላጃቼ ሁሌም በጥናጤ ይደግፉኛል በተጨማሪም ከልጅነቴ ጀምሮ ከጎኔ ያሉት ሰዎች ያበረተቱኛል” ስትል ትገልፃለች ። በዮኒቨርሲት ለማጥናት የወሰናችሁ ሃይድሮሎጂ ሲሆን ምክኒያቱ ደግሞ በሀገሯ ኒጄር ውስጥ የንፁሁ መጠጥ ውሀን ለሁሉም ለማደረስ የሚሰራውን ስራ ለማሳድግ ነው።

በሞሮኮ ፌዝ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪዎን ስቲዝ ፒ.ኤች.ዲ ዎን ደግሞ (በሃይድሮሎጂ) በፈረንሳዩ እስታርስ በርግ ዮኒቨርስቲ
ይዛለች። ሚያና በምሰራቸው ስራ ልክ በአይራ ንብረት ለወጠጥ እና በውሃ ብክለት ዙሪያ በቅርቡ በፎርብስ ድረገፅ
ላይ”30 Under 30 In Science 2020: Redefining Impossible From Rockets To Molecules” ውስጥ ተካታለች። በፈረንጆቹ 2019 ህዳረ ወረ አከባቢ በናሳ ሀላፊዎች አይን ውስጥ ልትገባ ችላለች። ይህ የሆነው ደግሞ ያኔ ባሳተመችው ፆሁፍ ብዙ ተቀባይነት ያገኘው በአከባቢ ጥበቃ አና በአየረ ንብረት ለወጥ እንዲሁም ተፆኖውን የካሊፎርኒያውን የደን መውደም ላይ በጥልቀት ያጠነጠነ ፆሁፍ ስለፃፈች ነው ።

ሚያና ለ ዘ አፍሪካ ሪፖርት እንደ ተናገረችው “ከልጅነቴ ጀምሮ ሁሌም ናሳ ውስጥ መስራት እፈልጋለሁ። ነገረ ግን በ
ዚንደር (ኒጄረ) ውስጥ ከተወለድክ የመረጃ እጦት አለ ይህ ችግር በኒያሚይ (የኒጄር ወና ከተማ) ውስጥም አለ።
ስለዚህም ይህ ህልም አለኝ ፣ ግን ኬት እንደምጀምር ወይም ምን አይነት መንገድ መከተል እንዳለብኝ አላውቅም ነበረ” ብላለች።

 እ.ኤ.አ በነሀሴ 27,2020 ከልጅነቷ ጀምሮ ስትምኝ እና ስታልም የነበረውን ናሳን ተቀላቅላለች። የኒጄሩ ፖሬዝዳንት “እሷ አሁን ለሀገራችን ኩራት ለኒጄር ወጣቶች ደግሞ ተምሳሌት ነች ” አበሮ የምስጋና መልእክት አስተላፏል። ሚያና በበኩላ “እንቅፋቶችን ሁሉ አልፌያለው ፣ እንደ ሚቻል አሳይቻለው ፣ አገሬንም ቢሆን አስከብሬያለሁ” ስትል ትገልፃለች በተጨማሪም “ልክ እንደኔ አይነት ሴት በዚንደሮ ተወልዳ የተወቀ ሳይኒቲስት በተወቀ ተቋም ውስጥ የመስራት እድሉ ዜሮ ነው ” ብላለች ።

ዛሬ ለይ ሚያና በናሳ የ “Gravity Recovery climate Experiment (GRACE) ሳተላይት ላይ የሚሰሩትን ቡድን ተቀላቅላለች። “የውሃ ዑደት እና የውሃ ሀብት ስነ ተፈጥሮውን በአይር ነብርት ለውጥ አገባብ የሒሳብ ሞዴልና ዳታ ከናሳ ሳተላይት የሚመጣውን መረጃ ለመረዳት እሞክራለው” ስትል ገልጸለች። አሁን ላይ በሀገሯ ከሚገኙ ኤን.ጂ.ኦ ጋር (በትምህርትና በሴቶች ነፃናት ለይ የሚሰራ) አብራ እየሰራች ትገኛለች ።


በመጨረሸም ዶክተር ፈዲጂ ዙዋና ሚያና ከሀገራ ኩራትና ምልክት አልፎ ፈርቀዳጅ አደሆነች እራሷ አሳይታለች። በኒጄር ዚንደር ተወልዳ ተስፋ በለመቁረጥና ተንክራ በመማር ይህው አሁን ለይ ናሳን ተቀላቅላለች። “እኔምፈልገው በይበልጥ ከኒጄር ሴቶች በሳይንሱ ዘረፍ እንዲሰሩና ልክ እንደኔ ተመሳሳይ መንገድ በመከተል እዚህ ናሳ ውስጥ ቶሎ እንዲቀላቀሉኝ ነው ” በማለት መልካም ምኞቷን አስተላልፋለች።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *