ኢትዮጵያ ሁለተኛዎን ሳተላይት አመጠቀች

Start

ልክ የዛሬ አመት ታህሳስ ወር ላይ ነበረ ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢቲ-አር-ኤስ-ኤስ-1 (ETRSS-1) የተባለውን ሳተላይት ወደ ምህዋርዎ ያመጠቀችው፡፡ ወደ ሃያ አንድ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን የተሳትፈውበት አና 70 ኪ.ግ የሚመዝን ሲሆን ወደ 6 ሚሊዮን ዶላር ወጪም ተደርጎበትል፡፡ ኢት-አር-ኤስ-ኤስ-1 ከመጠቀበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ጥቅሞች እያስገኘ ይገኛል፡፡ ሳተላይቱ የሚልከውን መረጃ የሚቆጣጠሩት ደግሞ የእንጦጦ የምርምር ማዕከል ቡድን ናቸው፡፡

ባሳለፍነው ማክሰኞ ደግሞ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ኢቲ-ስማርት-አር-ኤስ-ኤስ (ET-SMART-RSS) የተባለውን ሳተላይት ከቻይና ዌንቻንግ የማምጠቂያ ስፍራ ወደ ምህዋርዎ በተሳካ ሁኔታ አምጥቃለች፡፡ ይህ ሳተላይት ለአጉራችን አፈሪካ 42ኛው ወደ ሰማይ የመጠቀ ሳተላይት ሆኖዋል፡፡ በአለማችን ላይ ከ1957 ወዲህ የሩሲያው ከስፑትኒክ 1 ጀመሮ  እስከ 6000 የሚደርሱ ሳተላይቶች ወደ ሰማይ መጥቁል፡፡ ይህ የኢትዮጵያን ሁለተኛውን ሳተይት ያመጠቀው ሮኬት “ማርች ኤይት” የሚባል ስያሜ ያለው ሰሆን 356 ቶን የሚመዝን ነው፡፡

ኢት-ስማርት-አር-ኤስ-ኤስ ሳተላይት (ናኖ ተንቀሳቃቨ የመሬት መልከታ ሳተላይት) 8.9 ኪ.ግ የሚመዝን እንዲሁም 50.3 ሜትር ርዝማኔ ያለውና እስከ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪም የተደርገበት ነው፡፡ የዚህ ሳተላይት ዲዛይን በኢትዮጵያዊየን የወጣለት እና የቴክኒክን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች ደግሞ ከኢትዮጵያና ከቻይና በተወጣጡ ኢንጅነሮች በስምምነት የተሰራ ነው፡፡ ዶ/ር ሰለሞን በላይ (የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይነስ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት ዋና ደይሬክተር) ከኢትዮጵያን ሔርልድ (Ethiopian Herald) ጋር ባደረጉት ቆይታ በበኩለቸው “መጀመሪያ ከመጠቅነው ሳተላይት ብዙ ጥቅሞች እያገኘንበትና እየተማርንበትም ነው” ብለዋል፡፡ “ይህ ሁለተኛው ሳተላይት ደግሞ የተለያዩ መርጃዎችን እኛ/የመጀመሪያው ስተላይት/ ባልደርሰበት ቦታ ሄዶ የተለያዩ መረጃዎችን እንሚሰበስብ ይታመናል” ብለው አክለው ተናግረዎል፡፡

የሰታላይቱ ጥቅሞች ምንድን ናቸው ?

ሳተላይቶች ላንድ ሀገር ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ያስገኘሉ፡፡ እያስገኙም ይገኛሉ፡፡ ታዲያ ይህ የኢትዮጵያ አዲሱ ሳተላይት ለኢትዮጵያ ምን አይነት ጥቅም ይሰጣል ?

  • የመጀመሪያው እና ዋነኛው ጥቅም ሀገርችን ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ስትገዛ የነበረውን ዳታ ወይም( ስለ ኢትዮጵያ የምድረ-ገÒታ የሚገለÒ የተለያዩ መረጃዎችን) ያለምንም ክፍያ በራሱዋ ሳተላይት በነÑ ታገኛለች፡፡
  • በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዮችን የመሬት ገÒታን የማአድን ቦታዎችን ለማወቅ እንዲሁም የአየር ሁኔታን በቀላሉ ለመተንበይ የስችላል፡፡
  • የግብርና ስራን ለማሳለጥ እና ድርቅ ሊከሰት የሚችለበትን ቦታ ለይቶ በማሳወቅ ቅድመ-ጥንቃቄ እድናደርግ ይረደናል፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የሳተላይቱ ጥቅሞች ጥቂቶቹ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹ ጥቅሞች እነዚህ ናችው፡፡

በጥቅሉ ለመይት ያህል ኢትዮጵያ ባሳለፍነው አመት የመጀመሪያዋን ሳተይላት ኢቲ-አር-ኤስ-ኤ (ETRSS-1) ካመጠቀች ብሆላ ሁለተኛዋን ሳተላይት ባሳለፈው ማክሰኞ ታህሳስ 13 ላይ በተሳካ ሁኔታ አምጥቃለች፡፡ ይህ ሳተላይት ኢቲ-ስማርት-አር-ኤስ-ኤስ (ET-SMART-RSS) መጠሪያ ያለው ሲሆን ከቻይና ዌንቻንግ የማምጠቂያ ስፈራ በተሳካ ሁኔታ መጥቆል፡፡ ሳተላይቱ 8.9 ኪ.ግ የሚመዝን እና 50.3 ሜትር ርዝማኔ ያለው ሲሆን ከመሬታችን 700 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ሳተላይቱ የተለያዩ መረጃዎችን በመላክ ዘርፈ ብዙ ጥቀሞችን ያስገኛል ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አስር አመታት ወደ አስር የሚጠጉ ሳተላይቶችን ለማምጠቅ እቅድ ይዛለች፡፡     

Previous Story

ከተፈጥሮ ውጭ ያለው ዓለም የለም። አለ? የቅርብ ጊዜ የሳይንስ ምሁር አስተያየት እንደገና እንድንጠይቅ ያደርገናል ፡፡

Latest from News